ቡና • ክህሎት • ተስፋ

በእያንዳንዱ የቡና ስኒ፣ በራስ መተማመንን እንገነባለን፤ የሥራ ዕድሎችንም እንፈጥራለን።

ቀመሻ የምግብ ጥበብና የቡና ሳይንስ አካዳሚ ተግባራዊ የቡና ሙያ ስልጠና፣ ሙያዊ ክህሎት እና ለሥራ የሚያዘጋጅ ድጋፍ በመስጠት፣ ሰልጣኞች ወደ ሥራ ዓለም በዝግጅት እንዲገቡና የተሻለ የወደፊት ሕይወት እንዲገነቡ ያግዛል።

በቡና በኩል ዕድል መፍጠር

ብዙ ተሰጥኦና አቅም ያላቸው ሰዎች አቅማቸውን ወደ ሙያና የተሻለ የኑሮ ዕድል ለመቀየር የተለያዩ እንቅፋቶች ያጋጥሟቸዋል። ቀመሻ አካዳሚ ተግባራዊ የባሪስታ ሙያ ስልጠና፣ የሕይወትና የሥራ ክህሎቶች፣ እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ምክርና ድጋፍ ይሰጣል። በዚህም ሰልጣኞች ሙያዊ ብቃታቸውንና በራስ መተማመናቸውን አዳብረው፣ በቡና ዘርፍ የሥራ ዕድሎችን እንዲያገኙና የተሻለ ነገን እንዲፈጥሩ ያግዛል።

የምንሰጣቸው ስልጠናዎች

የቡና ሳይንስ መሠረቶች

የቡና አመጣጥን፣ የተለያዩ የጣዕም ባህሪያትን እና የኢትዮጵያ ቡናን በዓለም ዝነኛ ያደረጉ መሠረታዊ እውቀቶችን መረዳት።

☕ መሠረታዊ የባሪስታ ስልጠና

ተግባራዊ የባሪስታ ሙያ፣ የቡና አዘገጃጀት፣ የደንበኛ አገልግሎት እና በካፌ ውስጥ ለመሥራት የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ክህሎቶች።

💼 የሕይወትና የሥራ ክህሎት

በራስ መተማመንን፣ ውጤታማ የሙያዊ ግንኙነት ክህሎትን፣ ሙያዊ አስተሳሰብን እና ለሥራ ዝግጁነትን ለማዳበር የሚያግዝ ስልጠና።

ተግባራዊ ክህሎት ያግኙ።
በራስ መተማመንዎን ያዳብሩ።
የራስዎን የቡና ንግድ ይጀምሩ።

በቀመሻ አካዳሚ በተግባር የሚተገበር ስልጠና ያገኛሉ፤ በቡና አዘገጃጀትና አገልግሎት የሚያስፈልጉ እውቀትና ክህሎቶችን ያዳብራሉ፣ በራስዎ አቅምም የበለጠ ይተማመናሉ። ለተሻለ የሥራ ዕድል ለመዘጋጀት ወይም የራስዎን የቡና ቤት ንግድ ለመክፈት የሚፈልጉ ከሆነ፣ ቀመሻ አካዳሚ የሚያስፈልግዎትን ተግባራዊ ዝግጅት ይሰጥዎታል። ከሙያ ክህሎት በተጨማሪ የቡና ንግድዎን ለመጀመርና ለማሳደግ የሚያግዙ መሠረታዊ እውቀቶችንም ያገኛሉ።

ተጨማሪ መረጃ
Kemesha Academy students examining coffee

ወደ ቡና ሙያ የሚያመራ መንገድ

ተግባራዊ ስልጠና

በቡና ዘርፍ ልምድ ያለውና የCVA for Cuppers ሰርተፍኬት ባለው አሰልጣኝ የሚሰጥ፣ ተግባርን ከሙያዊ እውቀት ጋር ያጣመረ ጥራት ያለው ስልጠና።

የክህሎትና የግል እድገት

በስልጠናው ወቅት ሰልጣኞች ከደንበኞችና ከሥራ ባልደረቦች ጋር በጥሩ ሁኔታ የመግባባት ችሎታቸውን፣ በራስ መተማመናቸውን እና ሙያዊ ብቃታቸውን ያዳብራሉ።

ለሥራ ዝግጅት

ተማሪዎች ለሥራ ዝግጁ እንዲሆኑ ከማዘጋጀት በተጨማሪ፣ በካፌዎችና በቡና ዘርፍ ከሚገኙ የሥራ ዕድሎች ጋር እንዲገናኙ እናግዛለን።

አብሮነትና ድጋፍ

በቀመሻ አካዳሚ ብቻቸውን አይደሉም። ከስልጠናው መጀመሪያ እስከ ሥራ ዓለም ለመግባት እስከሚዘጋጁበት ጊዜ ድረስ፣ በራሳቸው አቅም እንዲተማመኑና ግባቸውን እንዲያሳኩ ማበረታቻ፣ ምክርና ተገቢውን ድጋፍ እንሰጣለን።

ዕድልን በጋራ እንፍጠር

የካፌ ባለቤት፣ በቡና ዘርፍ የሚሰሩ ባለሙያ ወይም የሙያ ስልጠናን የሚደግፉ ከሆኑ፣ የቀመሻ አካዳሚ አጋር ይሁኑ። ለሰልጣኞቻችን የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ሙያዊ ምክርና ድጋፍ በመስጠት ወይም ፕሮግራማችንን በመደገፍ፣ ብዙ ሰዎች ክህሎት እንዲያዳብሩና ወደ ሥራ ዓለም እንዲገቡ አብረውን መሥራት ይችላሉ።